የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከ4.5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ገለፀ

በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-24590 ኢት. ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ (ቦቴ) ተጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲጓጓዙ የነበሩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በሞጆ ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ ልዩ ቦታው አፍሪካ ነዳጅ ማደያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ከ4.5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሲሆን የተለያዩ ልባሽ ጨርቆች፣ ለማህበረሰቡ ጤና ጠንቅ የሆኑ ሲጋራዎችና ሺሻዎች መሆናቸውንም በአዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዋሪዮ ጉዮ ገልፀዋል፡፡

ኮንትሮባንዲስቶቹ ምንም እንኳን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ደብቀው ለማሳለፍ የተለያዩ ስልቶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም ፖሊስ ከህብረተሰቡ የሚደርሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግና የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ በቁጥጥር ስር እያዋላቸው መሆኑን በወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀረ-ኮንትሮባንድ ዳይሬክቶሬት፣ ሻለቃ ሁለት፣ ዲቪዥን ሁለት ሀይል አመራር ረዳት ኢንስፔክተር ዓሊ ሰይድ ገልፀዋል፡፡

ድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *