ፕሬዝዳንት ሲሲ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የማጥላላት ዘመቻ እንደተከፈተባቸው ተነገረ


የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የዳቦ ዋጋ ድጎማን ለማንሳት ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ፣ የሀገሪቱ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ የማጥላላት ዘመቻ ጀምረውባቸዋል፡፡

የቁጠባ እርምጃዎች አንዱ አካል ነው በማለት ሀገሪቱ በዳቦ ዋጋ ለማረጋጋት የምታድገውን ድጎማ ለማንሳት ሃሳብ እንዳላቸው የተናገሩትን ፕሬዝዳንት ሲሲን በመቃወም በርካታ ግብፃውያን በማህበራዊ ሚዲያ እያብጠለጠሏቸው ነው።

ሲሲ ይህንን የዋጋ ጭማሪ ይፋ ያደረጉት የምግብ ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡

በአረብኛ ሃሽታግ “ከቂጣው በቀር ሌላ ነገር” በሚል በትዊተር ላይ ከፍተኛ ዘመቻ በተጠቃሚዎች የተደረገበት ሲሆን ውሳኔው በግብፅ ውስጥ በጣም ደሀ ለሆኑ ዜጎች ስቃይን የሚያባብሰ ነው ብለዋል።

በ 2020-2021 በግብፅ አጠቃላይ በጀት የሂሳብ መግለጫ መሠረት ድጎማው 71 ሚሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎችን ይሸፍን ነበር።

የአቅርቦት ሚኒስቴር ኃላፊዎች የዳቦ ዋጋ ጭማሪን አስቀድመው ማጥናት መጀመራቸውንና በቅርቡም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ምክረ ሃሳብ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።

ሕዝባዊ አመጹ ቢነሳም ፣ የግብፅ ኢንዱስትሪዎች ፌዴሬሽን የገበሬዎች ማኅበር እና የዳቦ ጋጋሪዎች የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ በደስታ ተቀብለውታል ፣ “ዘግይቶ ቢመጣም እንኳ ድፍረት የተሞላበት ሃሳብ ነው” ብለውታል።

ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር የግብፅ አስተዳደር የድጎማ ዳቦን ክብደት ከ 110 ግራም ወደ 90 ግራም ዝቅ ማድረጉን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *