ይህንን ተከትሉም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍጋኒስታን መሪዎች ለትውልድ አገራቸው እንዲታገሉ አሳስበዋል።
በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የአፍጋኒስታን የጦር መሪዎች አንድ ላይ መሰብሰብ አለባቸው” ምክንያቱም የአፍጋኒስታን ወታደሮች ከታሊባን በቁጥር ይበልጣሉ እናም መታገል ይገባቸዋል ሲሉ አክለዋል።
እነሱ ለራሳቸው መዋጋት አለባቸው ፣ ለብሔራዊ ክብራቸው መታገል አለባቸው ነው ያሉት።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከአፍጋኒስታን ለመውጣት ባደረጉት ውሳኔ አልቁጭም ማለታቸው የሚታወስ ነው እንደ አልጀዚራ ዘገባ።
ዋሽንግተን ከ 20 ዓመታት በላይ በአፍጋኒስታን ቆይታዋ ከ 1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጓን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማጣቷን ጠቅሰዋል።
አሜሪካ ለአፍጋኒስታን ኃይሎች ከፍተኛ የአየር ድጋፍ ፣ ምግብ ፣ መሣሪያ እና ደመወዝ መስጠቷን ትቀጥላለችም ብለዋል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ነሐሴ 06 ቀን 2013 ዓ.ም
