ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን እና ነፃነትን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ቻይና በጥብቅ እንደምትደግፍ አስታወቀች


ቻይና ቋሚ አቋሟን በመጠበቀም በሰብዓዊ መብት ሰበብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ ኃይሎችን ትቃወማለች ብለዋል የቻይና የውጪ ጎዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዮ።

ቻይና በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር ተግባራዊ ትብብርን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን የውጪ ጎዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ የሚካሄደውን የቻይና አፍሪቃ ትብብር ፎረም ስብሰባ አጋጣሚን በመጠቀም ፤ በቻይና-አፍሪቃ ትብብር ላይ አዲስ መነሳሳትን ለማስፈን ዝግጁ መሆኗን የቻይና ግዛት ምክር ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ገልጸዋል።

ዋንግ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ቻይናና ኢትዮጵያ አንዳቸው የሌላው ሁለንተናዊ ስትራቴጂያዊ የትብብር አጋሮች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ፈተናዎችን አልፎ በየጊዜው እየጠነከረ መምጣቱን ተናግረዋል።
በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ወቅት ሁለቱ አገራት እርስ በእርስ በመረዳዳታቸው እና ወዳጅነታቸውን እንዳሳደጉ ዋንግ ገልፀዋል ፡፡

ቻይና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅትና ትብብርን ለመቀጠል እና የሁለቱን አገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል እንደ ሲጂቲኤን አፍሪቃ ዘገባ።

ዋንግ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሉዓላዊነትን እና ነፃነትን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ቻይና በጥብቅ እንደምትደግፍ ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔአበባ ሻምበል
ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *