የደብረ ማርቆስ ኤርፖርት ግንባታ ሊጀመር ነው::

የደብረ ማርቆስ ኤርፖርት ግንባታን ለማስጀመር የፕሮጀክቱን ሳይት ተቋራጩ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ መረከቡ ታዉቋል።

በሳይት ርክክቡ የደብረ ማርቆስ ከተማና የምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣የከተማዋ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣የጎዛምን ወረዳ የመሬት አጠቃቀም ባለሙያዎችና አመራሮች፣የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው የሚገነባበት ቦታ የተጎበኘ ሲሆን፣ አጠቃላይ አውሮፕላን ማረፊያው ሲገነባ ስለሚኖሩት ጠቀሜታና በውስጡ ስለሚኖሩት ፕሮጀክቶች ገለፃ ተደርጓል።

የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ በ137 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን፣ የአርሶ አደሮችን ካሳ ሳይጨምር 6 መቶ ሚሊዮን ብር ለግንባታው ብቻ ወጭ ይደረግበታል ተብሏል።

የአርሶ አደሮችን ካሳ የክልሉ መንግስት የሚከፍል ሲሆን 50 በመቶ የሚሆነው በጀት ተለቆ ለአርሶ አደሮች እየተከፈለ ሲሆን፣ ቀሪው በጀት በቅርቡ ተከፍሎ የአርሶ አደሮች ሰብል እንደተነሳ ግንባታው የሚጀምር ይሆናል ተብሏል።

የአየር ማረፊያው ግንባታ 913 ቀናት ወይም በሁለት አመት ተኩል እንደሚጠናቀቅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተገልጿል።

መረጃዉ የደብረ ማርቆስ ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤት ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሃሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *