የ 4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በማእከላዊ ምእራብ ሪጅን ተጀመረ።


ኢትዮ ቴሌኮም በማእከላዊ ምእራብ ሪጅን በሚገኙ አምስት ከተሞች የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን በይፋ አስጀምሯል።

አምቦ፣ ሰበታ ፣ ቡራዩ፣ ወሊሶ፣ ሆለታ የ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎቱ የተጀመረባቸው ከተሞች ናቸው።
በእነዚህ አካባቢዎች 134 ሺ ደንበኞች እንዳሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህወት ታምሩ በዚሁ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ አስታውቀዋል ።

የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትን በፍጥነት መጠቀም የሚያስችለውን የ 4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን እስካሁን በ 68 ከተሞች ማስጀምሩን አስታውቀዋል።

ይህንን አገልግሎት ተቋሙ በ 2014 በጀት ዓመት ተደራሽ ባልሆነባቸው 106 አካባቢዎች ላይ አጠናቆ አገልግሎቱን ለማስጀመር እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።

ይህንን ፈጣን የ 4 ጂ እና የአድቫንስድ አገልግሎትን ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የተሻለ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ፣ደንበኞች አገልግሎቱን ሊያገኙ የሚችሉበትን ግብአቶች ማቅረብ፣ እንዲሁም በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማዘመን እንደሚያስፈልግ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል ።

ተቋሙ በዚሁ በጀት ዓመትም የ 5 ጂ ኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስጀመር ማቀዱን ወ/ት ፍሬህይወት ተናግረዋል ።
ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹ ብዛት ከ 56.2 ሚሊየን በላይ መድረሱም ያስታወቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ የገባው ቴሌ ብር 8.9 ሚሊየን ደንበኞች እንደደረሱ ተነግሯል።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *