የኮቪድ 19 ክትባትን ከመንግስት የጤና ተቋማት ውጪ የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የጤና ሚኒስቴር አስጠነቀቀ::


የኮቪድ 19 ክትባትን በግል እያስከፈሉ የሚሰጡ አካላት ህገ ወጥ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ህብረተሰቡም ይሄንን ተከትሎ ራሱን ለአደጋ ማጋለጥ የለበትም ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የብሄራዊ ክትባት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ላቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ክትባቶቹ በእርዳታ የገቡ መሆናቸውን አስታውሰው፣ለህብረተሰቡ በመንግስታዊ ጤና ተቋማት ብቻ በነፃ የሚሰጡ ሆነው ሳለ ክፍያ እየተጠየቀ እንደሚሰጥ ሰምተን እያጣራን ነው ብለዋል፡፡


ከዚህም በተጨማሪ በህገ ወጥ መንገድ ክትባቶቹን ለመገበያየት መሞከር በአያያዙና በአወሳሰዱ ላይ እክል የሚፈጥር በመሆኑ ጉዳቱ የከፋ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
እስካሁን ለየተኛውም የግል ተቋም የኮቪድ 19 ክትባትን መስጠት እንዲችል ያልተከፋፈለ መሆኑን እና ፈቃድም እንዳልተሰጣቸው በማሳሰብ ለወደፊት በግል ጤና ተቋማት መሰጠት ሲጀመር ቀድመን የምናሳውቅ ይሆናል ነው ያሉት።


እስካሁን ግን ክትባት እንዲሰጥ ፈቃድ የተሰጠዉ የግል የህክምና ተቋም የለም ብለዉናል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃም በኢትዮጲያ ከ2 ነጥብ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸዉን ከጤና ሚንስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ነሃሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *