ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት አገራት አንዷ ናት አሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን

የቱርክ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ቱርክ በዘርፉ ከቀደምት ከሆኑ እና በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ሶስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ማለታቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል።

በሰሜን ምዕራብ ባለች አንድ ግዛት በተከናወነ ወታደራዊ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “ቱርክ ሰው አልባ በሆነው የአየር ላይ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ውስጥ ከሦስቱ እጅግ የተራቀቁ አገሮች አንዷ ሆናለች” ብለዋል።

ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቀዳሚ አገር ለመሆን ቆርጣ መነሳቷን ያስረዱት ኤርዶጋን ቱርክ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማዘጋጀት አለባት ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል።

የአገሪቱ ግብ በውጭ ሀገራት የአውሮፕላኖች ተልእኮ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ አጫጭር ማኮብኮቢያዎችን የሚይዙ እና በአውሮፕላን ተሸካሚዎች ላይ ሊያርፉ የሚችሉ የታጠቁ ድሮኖችን ማልማት ነው ብለዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *