ፑቲን አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያገኘችው ውጤት ‹ዜሮ› ነው ብለዋል

የአፍጋኒስታን የ 20 ዓመት ዘመቻ በአሳዛኝ ሁኔታ አብቅቷል እናም ዋሽንግተን ምንም አላገኘችም ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተችተዋል፡፡

የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን ውስጥ የነበረው ቆይታ ከንቱ ነበር ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል።

ፕሬዝደንት ፑቲን ከወጣቶች ጋር ባደረጎት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት “የአሜሪካ ወታደሮች በአፍጋኒስታን ለ 20 ዓመታት ኖረዋል ፣ እና በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ የአካባቢውን ህዝብ ሥልጣኔ ለማሳደግ ሳይሆን የኅብረተሰቡን የፖለቲካ አደረጃጀት ጨምሮ የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን ሞክረዋል ግን በእውነቱ አልተሳካላቸውም ብለዋል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የትኛውንም ህብረተሰብ ላይ ቢሆን “ከውጭ ማንኛውንም ነገር መጫን አይቻልም” ነው ያሉት፡፡

የሩሲያው መሪ ምዕራባውያን አገሮችን እሴቶቻቸውን በምዕራባዊ ባልሆኑ ሀገሮች ላይ ለመጫን በመሞከራቸው ትልቅ ውድቀት ገጥሟዋል ሲሉ አጣጥለዋቸዋል፡፡

ያንን ለሚያደርጉት አሜሪካ እና በአፍጋኒስታን ለሚኖሩ ሰዎች የበለጠ ውጤቱ እጅግ አሳዛኝ ፣ ከባድ ኪሳራ፣ ድምር ውጤቱም ዜሮ ነው ”ብለዋል ፑቲን።

ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *