ራሚስ ባንክ ከ700ሚሊየን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

በምስረታ ላይ የሚገኘው ራሚስ ባንክ እስካሁን ባለው ሂደት 724 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ሰብስቢያለሁ ብሏል፡፡

ባንኩ የእስላማዊ ፋይናንስ አገልግሎት ዘመናዊ የፋይናንስ አስተሳሰብ ከቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ውጤታማ የሆነ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱል ጀዋት መሀመድ እንደተናገሩት በምስረታ ሂደት 2 አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ለፈቃድ እንዲያመለክቱ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወሳል።

ራሚስ ባንክ በሚቀጥለው መስከረም 22 የምስረታ ጉባኤውን እንደሚያደርም አስታውቋል፡፡

እስካሁን ባለው ሂደት ውስጥ ከ6ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች አክሲዮን መግዛታቸውን ነው አቶ አብዱል ጀዋት የተናገሩት፡፡

ባንኩ ወደ ስራ ሲገባ ሰፊ የኢንቨስትመንት ክፍተት በሚታይበት የግብርናው ዘረፍ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *