16.7 ቶን የሚሆኑ የተለያዩ የምግብ ሸቀጦች የተቀመጠውን መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ አድርጓል።

ባለስልጣኑ የ2014 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች አቅርቧል።

በባለስልጣኑ የህዝብና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ዘለቀ በሶስት ወር ውስጥ 359 የምግብ አይነቶች ናሙና ተወስዶ የጥራት ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡

ከእነዚህም በላይ 328ቱ የሀገሪቱን ደረጃ በማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

16.7 ቶን የሚሆኑ የተለያዩ የምግብ ሸቀጦች ደግሞ መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በሩብ አመቱ ከአዲስ አበባ ምግብ መድሀኒትና ጤና ቁጥጥር ባለስልጣን እና ከኦሮሚያ ጤና ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በተደረገ የክትትልና ቁጥጥር በአዲስ አበባ 4300ኪሎ ግራም ቂቤና 65 ኩንታል በርበሬ ከባዕድ ነገር ጋር ተደባልቆ ተገኝቷል ሲሉም አቶ አበራ ተናግረዋል።

መቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *