በአማራ ክልል ሰባት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች በመድሀኒት እጥረት ችግር ላይ ወድቀዋል፡፡

በአማራ ክልል ከሰባት ሚሊየን በላይ የሚጠጉ ዜጎች በመድሀኒት እጥረት ምክንያት ለከፋ ችግር መዳረጋቸው ተገለፀ፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ህውሀት በያዛቸው አካባቢዎች ከ7ሚሊየን በላይ የሚጠጉ ዜጎች በመድሀኒት እጥረት እየተቸገሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የአማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጃለም እንደተናገሩት በክልሉ አሸባሪው የህወሀት ቡድን በወረራ በያዛቸው ስፍራዎች የሚገኙ ከሰባት ሚሊየን የሚበልጡ ዜጎች የመድሀኒት እጥረት አጋጥሟቸዋል ሲሉ ተናገረዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን በመድሀኒት አቅርቦት ብቻ ሳይሆን የጤና ስርአቱ ላይም ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ የክልሉ መንግስት በጦርነቱ ምክንያት ሊከሰት የሚችሉ በሽታዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበርያ ማእከል በማቋቋም ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *