የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሃን ፣ የትምህርት ና የልማት መድረክ በምህጻረ ቃሉ ካፎር አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ::

ካፎር ከ50 በላይ የኤክስፐርት ቡድኖችን፣ ከ1000 በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ያካተተና መረጃ ልውውጥ በማሳለጥ፣ አፍሪውካያን ወጣቶች ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉና ፣ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚተጋ ጥምረት ሲሆን ይህንን ዓላማውን ለማሳካት እንዲረዳው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬን የጥምረቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድሮጎ ሾሟል፡፡

አርቲስቱ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የካፎርን ዓላማ ተግባራዊ እንዲሰርጹ ማድረግ፣ ከአጋር ተቋማት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ማሳለጥ፣ የአድቮኬሲ ስራዎችን መስራትና የአፍሪካውያን ሥኬታማ ታሪኮች እንዲሰራጩ ለማገዝ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ እንደመረጠው አስታውቋል ፡፡

በሁለት አመታት ውስጥ ከሀገሩ ኢትዮጵያ አንስቶ በሌሎች አፍሪካ አገራት የሚገኙ ከአንድ ቢሊየን በላይ ለሚሆኑ አፍሪካውያንን ኑሮ ለመቀየር ካፎር ያነገበውን አላማ ለማሳካት የአፍካያንን ግንዛቤ በማስፋት የቅስቀሳ ስራዎችን ይሰራል ተብሏል።

“የበጎ ፈቃድ አምባሳደሩ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ለአፍሪካያን ወጣቶች፣ የክርክርና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት፣አርአያነት ያላቸውን አፍሪካውያን የስኬት ታሪኮች እንዲታተሙ በማድረግ፣ አፍካውያን ወጣቶች ለፈጠራ እንዲነሳሱ ማድረግ ይጠበቅበታል” ሲሉ የካፎር ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ላዋሌይ ኮሌ ተናግዋል፡፡

የጎዳና ልጆችን ለማገዝ ፣ እውቀትና ፈጠራ ላይ በመስራት አፍሪካውያን ከእርዳታና ድጋፍ ዛሬውኑ መላቀቅ አለባቸው ብዬ ስለማምን ነው፣የበጎ ፈቃድ አምባሳደርነቱን የተቀበልኩት ሲል ተናግሯል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *