በኢትዮጵያ በኮከብ ደረጃ የተካተቱም ሆነ ያልተካተቱ ሆቴሎች ቁጥር ከ2ሺህ አይበልጡም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በኮከብ ደረጃ የተካተቱም ሆነ ያልተካተቱ ሆቴሎች ቁጥር ከ2ሺህ እንደማይበልጡ የቱሪዝም ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር የአስር አመቱን እቅዱን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ጋር ባደረገው የምክክር መርሀ ግብር የተገለጸ ሲሆን በመጪው ታህሳስ ወር እንደ ሀገር የታሰበውን አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ንቅናቄ እውን ለማድረግ ሆቴሎች በበቂ ሁኔታ መኖር አለባቸው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ማግኝት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ መሰረተ ልማት ስራዎች እጅጉን ውስን መሆናቸው ነው የተነገረው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናንሲሴ ጫሊ በቱሪዝም ዘርፍ የአስር አመት እቅድ ላይ እንደተቀመጠው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር 7 ሚሊየን ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል፡፡

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቱሪስት እናመጣለን ሲባል ይህ የሆቴሎች እና ሌሎችም አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች አቅርቦት ከግንዛቤ ማስገባት አለብን ብለዋል፡፡

በአስር አመቱ የቱሪዝም ዘረፍ ከተያዙት እቅዶች መካከል ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች በመዲናዋ እና በክልል ከተሞች መገንባት ይገኝበታል ሲሉ አምባሳደሯ ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *