“ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ከኢትዮጵያ ጎን እቆማለሁ” በሚል ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ዜጎች የኢትዮጵያውያንን ድምጽ ለአለም ማህበረሰብ ለማስተጋባት ውይይት እያደረጉ ይገኛል፡፡

የ ጭላሎ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር በጊዮን ሆቴል “ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ከኢትዮጵያ ጎን እቆማለሁ” በሚል መርሃ ግብር ተካሔዷል፡፡

ከ30 የአፍሪካ አገራት በተገኙበት መድረክ ላይ ፣”አዲስ አበባ ሁለተኛዋ ቤታችን ናት፣ የአፍሪካዊያን ችግር በአፍሪካውያን ብቻ ይፈታል ፣ምእራባዊያን ሀገራት እና ሚዲያዎቻቸው በአፍሪካ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ማቆም አለባቸው “ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ የአፍሪካውያንን ጦርነት በድል አጠናቃለች፣ በመሆኑም በዜጎቿ የተገኝውን ድል ለማስጠበቅ ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን ሲሉ በውይይቱ የተካፈሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በኢትዮጵያዊያ እና በአፍሪካ ላይ የተቃጣውን የምስራባውያንን ጫና ለመከላከል የ “no more” ወይም ” የበቃ ንቅናቄ” በይፋ መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ከኢትዮጵያ ጎን እቆማለሁ በሚል በተዘጋጀው ውይይት መድረክ ላይ ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡

የውይይት መድረኩን ጭላሎ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *