የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ጦር ምስጋውን አቀረበ፡፡

የድርጅቱ የቀጠናው ተወካይ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ባለው ስነምግባር እና ህዝባዊ ወገንተኝነት ማመስገናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ጦሩ መሳሪያን አንግቦ ከመጠበቅም ባለፈ ህዝባዊ ወገንተኝነቱ እና ባለው አቅም ሁሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚረዳ በመሆኑም መመስገኑን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በሶማሊያ እና በሱዳን እየሆነ ላለው ነገር ልዩ ትኩረቱን ሰጥቶ እየተከታተለ እንደሚገኝ የገለፁት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሁለቱም ሃገራት የሌላ ወገንን ጣልቃ ገብነትን ኢትዮጵያ እንደምትቃወም ገልፀዋል፡፡

ከሃገራቱ በተጨማሪም የሱዳን እና የሶማሊያ ህዝብ ችግሮችን በራስ አቅም መፍታት እንደሚችሉ ኢትዮጵያ ታምናለች ያሉት አምባሳደሩ ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለመላው አፍሪካዊያን እንደሚያገለግልም አብራርተዋል፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *