የገንዘብ ሚኒስቴር በሁለት ወራት ውስጥ 70.6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አሳወቀ

የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት እና ህዳር ወራት ከሃገር ውስጥ ገቢ 70.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን እና የእቅዱን 89.3 ከመቶ ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት በመንግስት ገቢና ወጪ ረገድ ጤናማ የፊሲካል አስተዳደር ተግባራዊ መደረጉን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀሙ መገምገሙን አስታውቋል፡፡

በፌዴራል መንግስት፣ ከሀገር ውስጥና ከልማት አጋሮች ለመሰብሰብ የታቀደውን የመንግስት ገቢ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ያስታወሰው ሚኒቴሩ አፈጻጸሙም ‹‹መልካም›› ተብሎ እንደተገለፀም አስታውቋል፡፡

ከጥቅምት እስከ ታህሳስን ባሉት ወራትም ከበይነ-መንግሥታዊ ተቋማት (Multilateral) እና ከመንግሥታት ትብብር (Bilateral) የልማት አጋሮች በእርዳታና በብድር በድምሩ 364 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን እና 255.6 ሚሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ፈሰስ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ትርፍ ድርሻ 3.8 ቢሊዮን ብር ለማስብሳብ መቻሉን ያስታወቀው የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ የመንግስትን ወጪም በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በወራቱ ለፌዴራል መንግስት 73.3 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ይፋ ያደረገው መረጃው ለብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ወጪ የተደረገን 33.6 ቢሊዮን ብር ጨምሮ በድምሩ 106.9 ቢሊዮን ብር ለፌደራልና ለክልል መንግስታት ክፍያ መተላለፉን እወቁልኝ ብሏል፡፡

በተጨማሪም ትኩረት ለሚሰጣቸው የመንግስት ወጪ ፍላጎቶች ቅድሚያ በመስጠት የተገኘውን ጥሬ ገንዘብ በአግባቡ ማስተዳደር መቻሉን ያስታወቀው የገንዘብ ሚኒስቴር በእቅድ አፈጻጸሙ ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ደካማ ጎኖች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው በግምገማው ወቅት ተመክሪያለው ሲል በይፋዊ ገፁ ባሰፈረው መልእክት አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *