“በሂሩት አባቷ ማን ነው ? “ ፊልም ላይ ለተሳተፉ ተዋንያን ጥሪ ቀረበ፡፡


በቀዳማዊ አጼ ሃይለስላሴ ተመርቆ ለመጀመርያ ጊዜ ለህዝብ የተበረከተው ሂሩት አባቷ ማን ነው? ፊልም ላይ የተሳተፉ ተዋንያን አሁን ላይ የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል፡፡

የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እነዚህ ዜጎች የት እንደሚኖሩ በተለያዩ ጊዜያት ሲፈልግ እንደነበረ አስታውቋል፡፡
አሁንም በፊልሙ የተሳተፉ አካላት ወይም ቤተሰቦቻቸው እስከ ጥር 5ቀን 2014 አመት ድረስ ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያው ፊልም ሒሩት አባቷ ማን ነው ለዲያስፖራዎች ለእይታ ሊቀርብ ነው፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጥሪ ወደ ሀገር ቤት ለገቡት ዲያስፖራዎች በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያ ፊልም በግብዣነት ሊቀርብላቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በደራሲ ኢላላ ኢብሳ የተሰራው ሂሩት አባቷ ማን ነው ፊልም በ1957 አመት ነበር ለመጀመርያ ጊዜ ለእይታ የቀረበው፡፡
የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ዋና ዳሬክተር ብርሀኑ ሚሊቶ እንደተናገሩት በጊዜው ለፊልሙ 250ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገበት ተናግረዋል፡፡
ለበርካታ አመታት በብድር ምክንያት በልማት ባንክ ተይዞ እዳው ተከፍሎ ወደ ብሄራዊ ትያትር ቤት ገብቶ በ2012 አመት ዲጂታል ላይ ተደርጎ ዳግም ለእይታ መብቃቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ሂሩት አባቷ ማን ነው? ዲጂታላይዝ ለማድረግ 320ሺህ ብር ወጪ መደረጉን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ጥር 5ቀን 2014 አመት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለዲያስፖራዎች ለእይታ እንደሚቀርብ ነው ዳሬክተሩ የተናገሩት፡፡
ለዲስፖራዎች ከቀረበ በኃላ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለህዝቡ በ200 መቶ ብር ይቀርባል ተብሏል፡፡

ከዛሬ 57 አመት በፊት የተሰራው ሒሩት አባቷ ማነው ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን አሁን ላይ የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡
የፊልሙ ደራሲ ኢላላ ኢብሳ እንደዚሁም ሌሎችም ተዋንያን የነበሩ ኢትዮጵያዊያነን ወይም ቤተሰቦቻቸው ካሉበት ጥቆማ እንዲያደርጉ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አስታውቋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *