በአርጀንቲና ከ4 ቀን በፊት የተነሳው የሰደድ እሳት በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝን ብዝሀ-ሕይወት ማውደሙ ተገለጸ፡፡

በአርጀንተና ደቡባዊ ክፍል ቹበት(Chubut) በተባለችው ግዛት አቅረቢያ በሚገኝ ጫካ ላይ የተነሳው የሰደድ እሳት በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝን ብዝሀ- ሕይወት ማውደሙ የሀገሪቱ ባለስልጣናት መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

እሳቱ ያለማቋረጥ ለ 4 ቀንና ሌሊት እየነደደ በመቆየቱ ከ80 እስ 90 ሺህ ሄክታር መሬት የሚገኙ ዛፎችን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙ ብዝሀ-ሕይወት ላይ ውደመት ማድረሱን ባለስልጣናቱ ገልጸዋል፡፡

የዚህ አይነት አውዳሚ የሰደድ እሳት በሀገሪቱ ከዚህ በፊት ታይቶ እንደማይታወቅ የገለጹት ሃላፊዎቹ፤ ይህም ለእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ፈታኝ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

በቀጠለው የሰደድ እሳት እስካሁን በ90 ሺህ መሬት ላይ የነበሩት ለምለም ዛፎችና ሳሮች ወደ አመድነት ተቀይረዋል፤ አመዱም በነፋስ ተኗል፤ አካባቢውም ምደረ በዳ ከመሆኑ ባሻገር፣ በውስጡ የነበሩ ሀገር በቀል እፅዋት እና የዱር እንስሳትም መቃጠላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአርጀንቲና ከዚህ በፊት በተለያዩ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የሰደድ እሳት አደጋዎች እንደሚነሱ ያስታወቁት ባለስልጣኑ፤ ጉዳዩ ከአለም የአየር ንብረት ለውጥ መከሰት ጋር እንደሚያያዝ አመላክተዋል፡፡

በመሆኑም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለማስቀረት ሲሉ የተስማሙባቸውን አማራጮች ነገ ዛሬ ሳይሉ የማይተገብሯቸው ከሆነ ውድመቱ በአርጀንቲና ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር አስጠንቅቀዋል ሲል አናዶሉ ዘግቦታል፡፡

ጅብሪል መሀመድ
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *