“አክሱምን እና ላሊበላን የገነቡ አባቶች ያሉን ኢትዮጵያውያን፣ ታሪክ ቀምረን ከታሪክ መማር አቅቶን በተሳሳቱና በተዛነፉ ታሪኮች እርስ በርስ መግባባት አለመቻላችን አሳፋሪ ነው “ ታዬ ደንደኣ

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንዳኣ አክሱምን እና ላሊበላን የገነቡ አባቶች ያሉን ኢትዮጵያውያን አኩሪ ታሪክ ቢኖረንም ይህን ታሪክ ቀምረን፣ ከታሪክ መማር ሲገባን በተሳሳቱና በተዛነፉ ታሪኮች እርስ በርስ መግባባት እንኳን ቸግሮናል ብለዋል።

ሚንስትሩ ይህንን ያሉት “የታሪካዊነት አበርክቶ ለብሔራዊ መግባባት እና የታሪክ ምሁራን ሚና” የሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በሰላም ሚኒስቴር በጋራ በተሰናዳ ውይይት ላይ ነው።

ሰብአዊ ክብር፣ የግንባታ ሳይንስ ቀመር ቀድመን የምናውቅና ቀድመን የተረዳን ህዝቦች ስለ መሆናችን ብዙ ማሳያዎች ያሉን ህዝቦች ፣ በታሪክ እንኳ መስማማት አለመቻላችን አሳፋሪ የታሪካችን አካል በመሆኑ ይህን መሰል ውይይቶች የተሳሳቱ ትርክቶችን በማረምና በታሪክ ላይ የመግባባት ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

በመርህ ግብሩ ላይ የውይይት መነሻ የሆኑ የምርምር ጽሁፎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እና የኪነ ጥበብ ታሪክ ምሁሩ የቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው አማካኝነት ጽሁፎቹን ቀርበዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *