ኦፌኮ አመራሮቺ የታሰሩት በተዘጋጀ የሀሰት ክስ እና ከህግ ውጭ ነው ብሏል፡፡

ኦፌኮ ዛሬ በማህራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ መንግስት ሆን ብሎ ፓርቲውን ከፖለቲካ ምኅዳሩ ለማባረር የወሰነው  ለምርጫ ሲቃረብ  ነው ሲል ከሷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በግድ ከፖለቲካ ምህዳር ከተወገድን በኋላ ብዙ ነገር ተከስቷል ያለው መግለጫው ፤ ልንከላከለው የሞከርነው በጣም መጥፎው ሁኔታም ተፈጽሟል ነው ያለው።

በእስር ቤት ውስጥ ሆነን በአውዳሚው ጦርነት እና በተፈጠረው ሰብአዊ ውድመት የተጎዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ችግር በአሰቃቂ ሁኔታ ተመልክተናል። አገራችን  የውድቀት አፋፍ ላይ ስትወድቅ ከእስር ቤት ልንሰራው የምንችለው ነገር በጭንቀት ማልቀስ እና ለተሻለ ቀን መጸለይ ብቻ ነበር። በተለይ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግፍና  አሳዝኖናል ይላል መግለጫው።

ባለፉት 13 ወራት በሀገሪቱ እና በህዝቧ ላይ የደረሰውን አብዛኛው ጉዳት ለመቀልበስ በጣም ዘግይቶ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁንም ተጨማሪ ጥፋትን ለመከላከል፣ በዕርቅ ሰላም ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ እና አገሪቷን ለመገንባት የሚያስችል ትንሽ እድል እንዳለ እናምናለን። እንዲህ ዓይነቱ አድካሚ ሥራ የሁሉም ባለድርሻ አካላት እውነተኛ የፖለቲካ ፍላጎት እና የመልካም እምነት ተሳትፎን እንደሚጠይቅ ሳይገለጽ አይታልፍም ካለ በኃላ መግለጫው

በመሆኑም

– በተለይ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በትግራይ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች በሰላማዊና በድርድር እንዲፈቱ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል። በድርድር ሁሉን አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ ሁሉም ተዋጊ ቡድኖች የዜጎችን ፣ንብረት እና መሰረተ ልማቶችን ደህንነት እና ጥበቃ እንዲጠብቁ እንጠይቃለን ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እየተካሄደ ያለውን የሰላማዊ ትግል የሚጻረሩ ፣ የጥላቻ ቅስቀሳ እና ገደብ የለሽ የትጥቅ ጥሪ እንዲቃወሙ ጥሪ አቀርባለሁ ብሏል። የመገናኛ ብዙሃንም ወገናዊ ወሬዎችን ከማሰራጨት እና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳዎችን ከማስፋፋት በመቆጠብ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በተወዳጁ ኦሮሞ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ  ሞት ጥልቅ ሀዘን የተሰማን ሲሆን ከሀጫሉ  ግድያ በስተጀርባ ያለውን ሁኔታ እና ምክንያቶች በጥልቀት እና ተዓማኒነት ባለው አካል እንዲመረምር ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን።

በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና ሽፋን የተጨማለቀው የፍትህ ስርዓቱ ሀጫሉ በተገደለበት ምሽት ስለተከሰተው ነገር በቂ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም ሲል በመግለጫው ወቅሷል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስር ብሔርን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች የታሰሩትን ጨምሮ በርካታ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን፣ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላቶቹ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች – ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለንም ብሏል፡፡

ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *