የአዉሮፓ ህብረት ሩሲያን አስጠነቀቀ፡፡

ሩስያ ዩክሬን ላይ የምታደርገው ማንኛውም አይነት የተሳሳተ ስሌት አስከፊ ውጤት እንደሚከተለው ነዉ ህብረቱ ያሳሰበዉ፡፡

ህብረቱ በዩክሬን የሚራገፉ በርካታ የጦር መሳሪዎችንም ጭኖ ልኳል፡፡

በተጨማሪም የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን በምህጻሩ ኔቶ ከዚህ ቀደም ከላካቸው ተጨማሪ የጦር መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን እንደሚልክ አስታውቋል፡፡

አሜሪካም በዩክሬን የሚገኙ ዜጎቿ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ከማሳሰብ ባሻገር፣ ጥቂት የማይባሉ ወታደሮቿን ራሳቸውን ለግዳጅ እንዲያዘጋጁም ማሳሰቧ ተሰምቷል፡፡

ሩስያ በዩክሬን ጉዳይ እጇን በማስገባት መፈንቅለ-መንግስት ጭምር ለመሞከር ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች ሲል የወነጀላት የአውሮፓ ህብረት፣ ሞስኮ የትኛውንም አይነት የተሳሳተ እርምጃ ብትወስድ አፀፋው እጅግ የከፋ እንደሚሆንም አስጠንቅቋል፡፡

ሞስኮ ክሬሚያን ከተቆጣጠረችም በሁዋላ እውቅናን የነፈጋት የአውሮፓ ህብረት፣ ዳግም ወደ ዩክሬን የሚደረግን ወረራ በቸልታ እንማይመለከት እና ለአፀፋውም ከፍተኛ ዝግጅቶችን ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በአንፃሩ ሩስያ አውሮፓ እና አሜሪካ የሚያቀርቡባትን ውንጀላ ያጣጣለች ሲሆን ክሳቸው ሴራ መሆኑን እና በደጃፌ ኔቶን ለመትከል የሚደረግ ጥድፊያ እና ማዋከብ ነው ብላለች፡፡

ይህንኑ እንቅስቃሴም በቸልታ እንደማትመለከት ያስታወቀችው ሩስያ በእርሷም በኩል ለአፀፋው ዝግጅት ማጠናቀቋን አስታውቋለች፡፡

አብድልሰላም አንሳር
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *