አሜሪካ ከግብፅ ጋር የ2 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ስምምነት ፈጸመች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 12 ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮፕላኖችን ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ለግብፅ እንዲሸጥ አፅድቋል።

300 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የአየር መቃወሚያ ራዳር ሲስተሞች እና ሌሎች ተያያዥ መሳሪያዎችም ስምምነት ተደርጎባቸዋል፡፡

የጦር መሳሪያ ሽያጩ በቅርቡ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር በግብፅ የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ትችት ከሰነዘረ እና ካስጠነቀቀ በኃላ የተፈጸመ የመጀመሪያው ስምምነት መሆኑን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

በመስከረም ወር ዋሽንግተን ለካይሮ የተመደበ የ130 ሚሊየን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ማቋረጧ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ባለሥልጣናቱ ካይሮ የሰብአዊ መብት አያያዝን ማሻሻል አለመቻሏን እንደ ምክንያት ጠቅሰው ነበር፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *