የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ነፃ ሆኖ ዳግም እንዲደራጅ የተቋቋመው ግብረ ሃይል ስራውን ጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቋማዊ ነፃነት እንዲሳካ ለማገዝ የተዋቀረው ግብረ ሃይል ወደ ሥራ ገብቷል ፡፡

ዩኒቨርስቲውን ነፃ እና ተቋማዊ የማድረግ የለዉጥ ስራው ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ብቻም ሳይሆን ለሌሎች ዩኒቨርስቲዎችም ተቋማዊ ነጻነትን የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ከፍተኛ ተቋማትም የሚስፋፋ መሆኑም ተገልጿል።

መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተጎናፅፈው መስራት እንዲችሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቋማዊ ነፃነት ኖሮት መልሶ እንዲደራጅ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

በዉይይቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስራ አመራር ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና የተመረጡ የለዉጥ ሃዋሪያ አባላቶች ተሳትፈዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *