ፍትሐዊ የሆነ የሐብት ስርጭት እንዲኖር መሰረተ ሰፊ የኢንተርፕራይዝ ልማትን ማሳካት ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ

የኢንተርፕራይዝ ልማትን ማሳካት ካስፈለገ ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ስርጭት እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡

በአንድ አገር ላይ ፍትሐዊ የሆነ የሐብት ስርጭት እንዲኖር ከተፈለገ መሰረተ ሰፊ የሆነ የኢንተርፕራይዝ ልማትን ማሳካት ወሳኝ ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታውቀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ይህን ያሉት የዘርፉ ልማት ለአገር ኢኮኖሚ ባለው ሁለንተናዊ አስፈላጊነት ዙሪያ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የኢንተርፕራይዝ ልማት የስራ እድል መፍጠር ብቻ ተደርጎም ሊታይ የሚችል አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ በአንድ አገር ላይ ፍትሐዊ የሆነ የሐብት ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግ መሰረተ ሰፊ የሆነ ኢንተርፕራይዝ ልማትን እውን ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ዜጎች የተሻለ ሀብት የሚያመነጩበት፣ የተሻለ ምርት የሚያመርቱበት፣ ገቢ ምርትን የሚተኩበትና ኤክስፖርት ሊያደርጉ የሚችሉበትን እድል የምንፈጥረው ከጥቃቅን ጀምሮ እያደገ የሚመጣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ማሳካት ስንችል ነው ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት ትኩረት ሰቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

ዘርፉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ሁሉ የሚያንቀሳቅስ ሠፊ መስክ ነው ያሉት አቶ መላኩ አንድ ኢንተርፕራይዝ በምልዓት ውጤታማ መሆን የሚችለው እነዚህ ሁሉ ባለድርሻዎች በሃላፊነትና በጥበብ ዘርፉን ማገዝ ሲችሉ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የላኩልን መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *