ኔጌቲቭ የደም እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ በአራቱም የደም አይነቶች ኔጌቲቭ የደም እጥረት መኖሩን አስታውቋል፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደንበኞች የደም አሰባሰብ አስተባባሪ ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በስድስት ወራቶች ውስጥ 188ሺህ ከረጢት ደም እንደሀገር መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል፡፡

በበጀት አመቱ ስድስት ወራቶች ውስጥ 198ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 188ሺህ ያህል ከረጢት ደም ሰብስበናል ብለዋል፡፡

እንደሀገር የተደቀኑብንን ችግሮች ተቋቁመን ይህንን ያህል ደም መሰብሰብ መቻላችን ዋነኛ ምክንያት የህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ታክሎበት እንደሆነ ዳሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ባለፉት ስድስት እና ከዛ በላይ በሆኑ ወራቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ የነበረው የደም ልገሳ በአሁኑ ሰአት መቀዛቀዝ ማሳየቱንም ነው የተነገረው፡፡

እንደ ፕሌትሌት ያሉ የደም አይነቶች አሁንም እጥረት እንዳለ የተናገሩት ዶ/ር ተመስገን ህዝቡ አሁንም ደም መለገሱን እንዲቀጥል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ ከተሰበሰበው የደም መጠን አብዛኛው አገልግሎት ላይ መዋሉን ዶ/ር ተመስገን ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *