በድሬዳዋ ከተማ በቀረጥ እና ከቀረጥ ነጻ ከውጭ በሚገቡ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ ተመሳሳይ መሆኑ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነባቸው የከተማ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስታውቋል

ቀረጥ የተከፈለባቸውና እና ከቀረጥ ነጻ ከውጭ በሚገቡ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ ተመሳሳይ መሆኑ በህጋዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱ አስመጭ እና ላኪ ነጋዴዎች ፈተና መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ የህገወጥ ንግድ እንቅስቃሴ እንደሚካሄድ እና የቁጥጥር ስራውም ዝቅተኛ በመሆኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ገልጾ ነበር፡፡

ህገወጥ ንግድ ከሚካሄድባቸው ምርቶች መካከል ጫት እና ነዳጅ ከፍተኛውን ደረጃ እንደሚይዙ ኮሚቴው ያረጋገጠ ሲሆን ችግሩን ለመቀነስ የቁጥጥር ስርዓቱ መጠናከር እና መዘመን እናዳለበት አመላክቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ከንግድ እና ማህብራት ዘርፍ ምክር ቤት ተወካይ አባላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት፣ የህገወጥ ንግድ ከፍተኛ ጫና እያሳሣደረ እንደሆነ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ለችግሩ ትኩረት በመስጠት ተቀናጅተው ከመስራት አንጻር ውስንነት የሚታይባቸው እንደሆነ ማረጋገጡን አስታውቋል።

የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ተወካይ አባል እንዳነሱትም የህገወጥ ንግድ ላይ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ያለው ቅንጅታዊ ስራ ክፈትት እንዳለበት በመጠቆም፣ በቀረጥ እና ከቀረጥ ነጻ ከውጭ የሚገቡ የፍጆታ ምርቶች ላይ የሚስተዋለው የዋጋ ሁኔታን ያለውን ሁኔታ የቁጥጥር ስርዓቱ በማጠናከር እና በማዘመን መከላከል እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ማሳሰቡን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *