በጌዴኦ ዞን ከ70 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስነ አካላዊና ስነ ሕይወታዊ ስራ ሊሸፈን ነው ተባለ፡፡

የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በሁሉም በግብርና ዘርፎች በማቀናጀት የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እንደሚሰራ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ በተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ በዘርፉ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን በተያዘዉ በጀት አመት በዞኑ በ133 ንኡስ ተፋሰስ ስር ከ70 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት መታቀዱን የሚናገሩት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ዝናቡ ወልዴ ናቸዉ፡፡

የአየር ንብረት ለዉጥ አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ወቅት ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥና የአርሶ አደሩን ሕይዎት ለማሻሻል አፈርና ዉሃ አጠቃቀማችን ላይ ያለዉን ግንዛቤ ማስተካከል እንደሚገባም አቶ ዝናቡ ወልዴ ገልጸዋል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *