በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎባ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው የደረሰው በጎባ ወረዳ ልዩ ስሙ ገንዳ ሪራ በተባለ ሥፍራ መሆኑን በጎባ ፖሊስ የሰላም ማረጋገጥ ዲቪዥን ረዳት ኢንስፔክተር ሙክታር ሁሴን ተናግረዋል።

አደጋው ከደሎ መና ወደ ሮቤ ዶዘር እየጎተተ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ክሬን ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሮቤ ወደ ደሎ መና በመጓዝ ላይ ከነበረው የፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል።

በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ ዘጠኝ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህይወት ሲያልፍ ፥ በአራቱ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱም ተገልጸዋል።

በአደጋው ክሬኑን ሲያሽከረክር የነበረው ረዳት በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ሙክታር ተናግረዋል።አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን ፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል።

ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ጎባ ሪፌራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *