ዛሬ ከ64 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የእህል ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን ሰምተናል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል ተብሎ የነበረው የእህል ማዳበሪያ ከጨረታና ግዢ ጋር በተያያዘ መዘግየቱ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ የመጀመሪያዋ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን ከግብርና ሚንስትር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ሁለተኛውን ዙር የማዳበሪያ ጭነት የያዘችው መርከብ አስከ ጥር 30 ድረስ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ እና ማዳበሪያው በህብረት ስራ ማህበራት በኩል በፍጥነት እንዲሰራጭ እንደሚሰራም ታውቋል፡፡

የእህል ማዳበሪያ ዋጋ በአለምአቀፍ ገበያ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየቱ የተነሳ አቅራቢ ኩባያዎችን ለመምረጥ የተደረጉ ጨረታዎች አለመሳካታቸው ለመዘግየቱ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በዛሬው እለት በጅቡቲ ወደብ የደረሰው የመጀመሪያው ዙር የእህል ማዳበሪያ መጠኑ 64ሺ 670 ሜትሪክ ቶን ሲሆን በዚሁ ሳምንትም ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዝ እንደሚጀመርም የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ሶፍያ ካሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ዳዊት አስታጥቄ
ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *