የአውሮፓ ህብረት አገራት ከ13 ሚሊየን ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረጉ።

በርክክብ ስነስርአቱ ላይ ዶክተር ሊያ ታደሰ የተደረገው ድጋፍ የክትባት አቅርቦትን እንደሚያሳድግ የገለፁ ሲሆን ለበሽታው መገታትና መከላከል ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል። 56

ድጋፍ ያደረጉት ሰድስት ሀገራት ፈርንሳይ፣ ፊላንድ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ፣ ጣልያን እና ስዊድን ሲሆኑ በአጠቃላይ 13,096,800 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ መገኘቱም ታውቀዋል።

በአጠቃላይ ከዚህ ቀደም ከጀርመንና ፓርቹጋል መንግስታት የተገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት አገራት 24,000,000 ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ አግኝታለች።

በርክክብ ስነስርኣቱ የሀገራቱ አምባሳደሮች፣ የኢምባሲ ተወካዮች፣ የዩኒሴፍ ተጠሪዎች የተገኙ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ክትባቱን ተደራሽ የማድረግ ስራ ለበሽታው ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረትና ቁርጠኝነት ያመለክታል ብለዋል።

በአገሪቱ ክትባቱን መስጠት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ የገለፁት ሚኒስትሯ ክትባቱ በአገሪቱ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት ባሉ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑ አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ ለተደገው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ፣ የክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት ያደርሳል የሚል ፍርሃትን የሚድያ አማራጮችን በመጠቀም መልእክቶች ተቀርፀው ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *