የአፍሪካ ህብረት 35ተኛው የመሪዎች ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርአት እየተካሄደ ይገኛል ፡፡

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የህብረቱ ኮሚሽነር ሙሳፋኪ ማሃማት ዋና ዋና ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተው ሰፊ ውይይት እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን በተለይም በአህጉሪቱ እየተደጋገመ የመጣው የመፈንቅለመንግስት የደህንነት ስጋት የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ እንዲሁም በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ ጠይቃ የነበረችውን የእስራኤልን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የእርስ በእርስ ግንኙነታችን በድጋሚ ሊጤን ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ በየቀጠናው ያለው የየሃገራት ግንኙነት እየሻከረ መምጣት አስጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር ከ2 አመታት በላይ ህብረቱ ሳይሰበሰብ መቅረቱን አስታውሰው የኮሮና ቫይረስ ከነጠቀው የሰው ህይወት በተጨማሪም ያልተገባ የቫይረሱ መከላከያ ክትባት ስርጭት እና ሌሎች ፈተናዎችን ደቅኖብን ነበር ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ አህጉራችን በትኩረት መስራት ይገባታል ያሉትጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገራችን የተከናወነውን የመስኖ ስራዎች ስኬትን እንደአብነት አንስተዋል የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የአየር ንብረት ለውጥን ያነሱት ዶ/ር አብይ ተፅዕኗቸው ከፍተኛ እንደበርም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም አህጉሪቱ ተመድ እራሱን እንዲያድስ መጠየቅ እንዳለባት ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ70 አመት የተሻገረ እድሜ ያለው ድርጅቱ በሚያደርገው ሪፎርም ለአፍሪካ ቢያንስ 2 ቋሚ እና 5 የተለዋጭ አባልነት ቦታ እንደሚያስፈልጋትም በቀጥታ ስርጭት በተላለፈው የመሪዎቹ ጉባኤ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ የሆነ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ያስፈልጋታል ያሉ ዶ/ር አብይ አህመድ የራሳችንን ጉዳይ እራሳችን ልንናገር ይገባናል ብለዋል፡፡
በጉባኤው ላይ የተመድ ዋና ፃሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም ንግግር አድርገዋል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
ጥር 28 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *