አሠልጣኝ ጳውሎስ ተሽሏቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን የመጨረሻ ጨዋታ የሆነው የመከላከያ እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ በመከላከያ 3-1 አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ ይታወቃል።

ወልቂጤ 5ኛው ደቂቃ ላይ ጫላ ተሸታ ባስቆጠራት ጎል መሪነቱን ቢጨብጥም በ10ኛው ደቂቃ ዋና አሠልጣኙ ጳውሎስ ጌታቸውን በህመም አጥቷል፡፡

አሠልጣኙ ዛሬ ጠዋት ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ የጤንነታቸው ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ያጋጠማቸው የጤና እክል ድንገተኛ ሳይሆን ከሰሞኑን ተከስቶባቸው የነበረው የታይፈስ እና ታይፎድ ህመም አቅም ስላሳጣቸው ጉልበት እንደከዳቸው ገልጸዋል፡፡

አሰልጣኙ አሁንም በድሬ ህክምና ማዕከል ውስጥ እንደሚገኙ እና ተገቢውን ህክምና ማግኘታቸውን እና እየተሰጣቸው የሚገኘውን ግሉኮስ ጨርሰው ሲበረቱ ወደ ሆቴላቸው እንደሚመለሱም ተናግረዋል፡፡

አቤል ጀቤሳ
ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.