የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ መምጣቱ የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ

የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ መምጣቱ እና በአጠቃላይ የደረሰብን የሞራል ክስረት ከፍተኛ እንደሆነ ሚንስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

የእኔ ክልል ተማሪዎች ማለፍ አለባቸው በሚል በተቋም ደረጃ የፈተና ወረቀቶችን በመስረቅና መልስ በመስጠት ጭምር ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸው ፣ የትምህርት ሲስተሙ ጥራት ተዓማኒነት ከፍተኛ ጥያቄ ዉስጥ መግባቱን አንስተዋል፡፡

አንድ ሰዉ በዚህ የትምህርት ስርዓት ዉስጥ አልፎ ድግሪ ሲያገኝ ድግሪዉ ለማህበረሰብ መስጠት ያለበትን መልዕክት ይሰጣል ወይ፣ ትርጉም ያለዉ መመዘኛስ ይኖረዉ ይሆን መባል አለበት ይህንን ማድረግ የሚቻለዉ ግን ሲስተሙ ተዓማኒነቱ የተጠበቀ ከሆነ ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡

‘’ግማሹ ለፍቶ ጥሮ ዉጤት እየያዘ ፣ ሌላዉ ደግሞ ከድግሪ ፋብሪካዎች ድግሪ እየተቀበለ የሚያልፍበት ሁኔታ ካለ ችግሩ የተወሰኑ ሰዎች ማለፍ ሳይሆን ፣ ችግሩ የትምህርት ጥራቱ ላይ ነዉ’’ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ፈተና የሰዎችን ክህሎት እና ታታሪነት መለኪያ መሆኑ ቀርቶ ተሰርቆ ና መልስ ተሰጥቶ የሚመጣ ዉጤት ምዘና አያሟላም፣ ተዓማኒነትም አይኖረዉም ብለዋል፡፡

“የትምህርት ተቋማት ምዘና ተደርጎባቸዉ ሰርተፊኬት ይስጡ በሚባልበት ሁኔታ በተለይ ለግል ትምህርት ቤቶች የስራ ሰርተፊኬት የሚሰጠዉ በችሎታቸዉ ሳይሆን በጉቦ ከሆነ ሲስተሙ ፈርሷል ይህንንም ሁላችንም ነው የምናዉቀዉ ነገርግን ፊትለፊት ስለማንነጋገርበትም ስር የሰደደ መፍትሄ ልንፈልግለት ያልቻልነዉ ጉዳይ ነዉ“ ብለዋል፡፡

የትምህርት ስርዓቱን ተዓማኒነት ጥያቄ ዉስጥ የሚከት አካሄድ በጣም ተንሰራፍቷል ያሉት ሚንስትሩ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል እንደዚህ ያሉ አሰራሮችን ማስቆም ና የሲስተሙን ተዓማኒነት ችግር ዉስጥ የሚከቱ ጉዳዮችን ከስር መሰረታቸዉ መፍታት አለብን ሲሉ ለሰው ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል፡፡

እስከዳር ግርማ
የካቲት 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *