ቱርክ ሶስት የምእራባዊያን መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስጠንቀቂያ ማውጣቷ ታውቋል፡፡

ቱርክ ማስጠንቀቂውን ያወጣችው ከአገልግሎት ፍቃድ ጋር በተያያዘ ስለመሆኑም ተሰምቷል፡፡

የቱርክ የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት አውጥቶታል የተባለው ማስጠንቀቂያው በዋሽንግተን ስርጭቱን የሚያደርገውን የአሜሪካ ድምጽን (VOA) እንደሚያጠቃልል ታውቋል፡፡

በ2021 እንደወጣ መረጃ የአለም የፕረስ ነፃነት የሃገራት ምዘና ደረጃ ላይ ቱርክ ከ18 ተመዛኝ ሃገራት ውስጥ 154ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

በተጨማሪም የሃገሪቱ ህገመንግስት አንቀፅ 28 ላይ ለፕረስ ነፃነት የማይገረሰስ መብት የሰጠ ቢሆንም ቱርክ ከሳንሱር ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስሟ ሲነሳ ይሰማል፡፡

ቱርክ በአየር ክልሏ አገልግሎታቸውን ማሰራጨት የሚያስችላቸውን ፈቃድ እንዲያወጡ ያስጠነቀቀቻቸው መገናኛ ብዙሃን ዝርዝር ውስጥ በፈረንሳይ የሚገኘውን ዩሮ ኒውስ እና በጀርመን ታክስ ከፋዮች የሚተዳደር ስለመሆኑ የሚነገርለትን ዶቼ ቬሌን ያጠቃለለ መሆኑን አርቲ ዘግቧል፡፡

አብዱሰላም አንሳር
የካቲት 03 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *