በአዲስ አበባ 74 መኪኖች ተሰርቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ በስድስት ወራት ወስጥ 74 ያህል መኪኖች መሰረቃቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በአንድ ወቅት ለአዲስ አበባ ከተማ ፈተና ሆኖ የቆየው የመኪና ስርቆት ጉዳይ አሁንም መፍትሄ አልተገኘለትም ነው የተባለው፡፡

በመዲናዋ ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻም 74 ያህል ኪኖች መሰረቃቸውን የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሁለት ጭማሪ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መኪኖቹ አብዛኛዎቹ የሚሰረቁት ለባለቤቱ ቅርብ በሚባሉ ሰዎች አማካኝነት እንደሆነም ነው የተነገረው፤ እንደዚሁም በሰዎቹ እንዝላልነት እና ቸልተኝነት ነው ስርቆቱ የሚፈጸመው ሲል ፖሊስ ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

መኪና አጣቢዎችም ለመኪና ስርቆቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ነው የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገሩት፡፡

የመኪና ስርቆት ከባድ ከሚባሉ የወንጀል አይነቶች እንደሚመደብ የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካው አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ 13 ከመቶ መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡

የከባድ ወንጀሎች ቁጥር የቀነሰበት ዋነኛ ምክንያት ፖሊስ እና ህብረተሰቡ ተቀናጅተው በመስራታቸው ነው ተብሏል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *