‹‹የታላቁ ኢድ ስግደት በኢትዮጵያ በሚቀጥለው ረመዳን ይደረጋል›› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

በሚቀጥለው ረመዳን ታላቁ የኢድ ስግደት በኢትዮጵያ ይደረጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከፓርላማ አባላት በርካታ ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች ተነስቶላቸው በአሁን ሰዓት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲያክሉም ‹‹ ብዙ የአረብ ሃገራት በቂ ሙስሊም ያለን አይመስላቸውም ፤ ግማሽ የሚያህለው ሙስሊም ያለበት ሃገር በእምነቱ ጠንካራ የሆነ እሴት ያለው ነው›› ብለዋል፡፡

ዲያስፖራውም ኢድን በኢትዮጵያ መጥቶ እንዲያከብርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *