በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡

ሩስያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በትምህርት ዩክሬን የሚገኙ ኢትጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከሚገኙበት ቤት እየተንቀሳቀሱ አይደለም ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ስጋት የገባው ጀርመን የሚገኝው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያዊያኑ ካሉበት ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ትዛዝ ሰጥቷል፡፡

ኤምባሲው በድረገጹ ላይ ባወጣው መረጃ መሰረት ዜጎች ኤምባሲው በሚሰጣቸው ትዛዝ መሰረት እንዲንቀሳቀሱ አሳስቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በገጠማችሁ ችግር ምክንያት ከመንቀሣቀሣችሁ በፊት በማንኛውም ጊዜ ሞባይል ስልክ ቁጥር እና በኢሜል አማካኝነት ከኢምባሲያችን ጋር ተመካከሩ ሲል መልእክቱን አስተላልፏል፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *