ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን ጋር አስቸኳይ ድርድር እንዲደረግ ጠየቀች።

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የመጀመርያው ምዕራፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሥራ መጀመሯን በይፋ መግለጿን ተከትሎ ግብፅ በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ድርድር እንዲካሄድ ለአፍሪካ ኅብረት ጥሪ አቅርባለች።

በመጋቢት 2015 በሶስቱ ሀገራት መካከል በካርቱም መካከል የተፈረመ የመርሆች ስምምነት መሰረት እንዲደረግ መጠየቋ ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

ባለፈው እሁድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከ13 ተርባይኖች አንዱን በማንቀሳቀስ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት ሂደትን ማስጀመራቸው የሚታወስ ነው።

የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለአልአረቢ አልጃዲድ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን ጋር በመተባበር በሶስቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ድርድር የመምራት ኃላፊነት የተጣለበትን የባለሙያዎች ኮሚቴ የማዋቀሩን ሂደት እያደናቀፈ ነው ሲሉ ይከሳሉ፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ. በ2015 በወጣው የመርሆች ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ የገባችውን ቃል ጥሳለች ሲል ይከሳል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳስታወቀው “ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተፈረመው በ2015 የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት የተገባውን ቃል ይጥሳል” ብሏል።

ያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.