በ5 ሚሊየን ዶላር የተገነባ ግሎኬር የተሰኘ መድሃኒት ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡

በቂሊንጦ ኢንደስትሪ ዞን ውስጥ የተገነባው ፋብሪካው በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የመድሃኒት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በሃገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች የምትገኝ ሲሆን ግሎኬር የመድሃኒት ፋብሪካ ለዚሁ የድርሻውን እንደሚወጣም ተጠቁሟል፡፡

ፋብሪካው በአመት 600 ሚሊየን ታብሌት እና 7 ሚሊየን ፈሳሽ (ሽሮፕ) መድሃኒቶችን እንደሚያመርት ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚኒኪሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል ፤ 60 ለሚሆኑ ሰዎችም የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ግሎኬር በአመቱ መጨረሻም እስከ 250 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ፋብሪካው የ2ተኛ እና ሶስተኛ ምእራፍ ግንባታዎችን እያከናወነ ሲሆን 4.5 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *