የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት መሰረታዊ ምግቦች ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ጣለ፡፡

የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቦዩን ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸውን መሰረታዊ የምግብ ምርቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ መጣላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ስኳር፣ ዘይት፣ ፓስታ እና ስንዴ እገዳው ካካተታቸው የምግብ ሸቀጦች መካካከል ይገኙበታል።

የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የታሸጉ የስጋ ምርቶችንም ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይከለክላል ሲል የሃገሪቱ የዜና ወኪል ገልጿል።

የእገዳው ምክንያት ምን እንደሆነ ባይገለጽም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩክሬን ግጭት ምክንያት እንደ ስንዴ ያሉ መሠረታዊ ምግቦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ በሃገሪቱ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል፡፡

ስንዴን በብዛት ከዩክሬን ከሚያስመጡ ሃገራት ውስጥ አንዷየሆነችው ግብፅ ባለፈው ሳምንት ለሶስት ወራት ያህል ስንዴ፣ ዱቄት፣ ፓስታ እና ጥራጥሬ ለውጭ ገበያ እንዳይቀርብ መከልከሏ የሚታወስ ነው።

መሳይ ገ/መድህን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *