በመላው አለም 2.2 ቢሊዮን ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሀ አያገኙም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ አደረገ ፡፡


በአለማችን ከሚገኙ 7.8 ቢሊዮን ህዝብ መካከል 2.2 ቢሊዮን ያክሉ ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሀ እንደማያገኝ ድርጅቱ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ዘንደሮም ለ28ኛ ጊዜ የአለም የውሀ ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ከፈረንጆቹ 1993 አንስቶ እየተከበረ የሚገኝው የአለም የውሀ ቀን በአፍሪካ ደረጃ በጋና አክራ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ይህንኑ ሁነት ለመካፈል በፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተመራ ሉኡክ ወደ አክራ አቅንቷል፡፡

እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከንጹህ መጠጥ ዉሃ እጦት በሚመጡ በሽታዎች ሳቢያ በዓለም ላይ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ 289 ሚሊዮን ህፃናት ይሞታሉ ይላል ሪፖርቱ።

ኢትዮጵያ የዉሃ አቅርቦትን እያሻሻሉ ካሉ 10 ሀገራት ዉስጥ 7ተኛ ደረጃ ላይ ብትሆንም ንፁህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት በመኖሪያ አቅራቢያ ከማያገኙ 10 ሀገራት መካከል 2ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ፣ በጣም ዝቅተኛ የዉሃ አቅርቦት ካላቸዉ ሀገራት ደግሞ በ 4ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በሀገሪቱ 39 በመቶ የሚሆነዉ ህዝብ ብቻ በመኖሪያ አቅራቢያዉ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ያገኛል ያሉት በኢትዮጵያ የወተር ኤድ ሃላሪ የሆኑት ካትሪን

ክሪደር አቅርቦቱን ለማሻሻል መንግስት በርትቶ ሊሰራ ይገባል ነዉ ያሉት።
በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ የንፁህ ውሃ አቅርቦት የለውም።

ዋተር ኤይድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ይህንን እንዲል ያስቻለው፤ ሰዎች ምን ያህል ውሃን በቤታቸው ውስጥ ያገኛሉ ወይም ንፁህ ውሃን ለመቅዳት ከግማሽ ሰዓት በላይ በእግራቸው ለመጓዝ ይገደዳሉ የሚለውን በማጥናት ነው።

ንፁህ ውሃን የማያገኙ ሰዎችን ብዛትን በተመለከተ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ቻይናዊያንና ሕንዳዊያን ናቸው።
ነገር ግን ሃገሮች ካላቸው የህዝብ ቁጥር አንፃር በመቶኛ ሲሰላ የውሃ ችግር በተለይ በአፍሪካ የከፋ ነው።

በንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ሃገራትም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያና የዲሞክራቲክ ኮንጎ ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2030 ንፁህ የመጠጥ ዉሃና ንፅህና ለእያንዳንዱ ሰዉ ለማዳረስ የያዘዉን ግብ ለማሳካት በሚፈለገዉ ፍጥነትና መሻሻል እየሄደ እንዳልሆነ ነው ያስታወቀው፡፡

መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም
ሔኖክ ወልደገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *