በሳምንቱ መጨረሻ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ በሁለት ቀናት ውስጥ በተከሰቱ የእሳት አደጋዎች በንበረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ እሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
አንደኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በኦሮምያ ልዪ ዞን አሸዋ ሜዳ በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰው ነው ተብሏል፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን ሌላኛው የእሳት አደጋ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት አወልያ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሶስተኛው የእሳት አደጋ የተከሰተው ደግሞ በትላንትናው እለት በኦሮሚያ ልዩ ዞን አሸዋ ሜዳ በተመሳሳይ በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ሲሆን በነዚህ አደጋዎች ምክንያትም ከ2ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ብለውናል፡፡

አደጋዎቹን ለመቆጣጠር 40ሺህ ሊትር ውሀ አገልግሎት ላይ መዋሉንም አቶ ንጋቱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

መጋቢት 19፣ቀን 2014
ሔኖክ ወ/ ገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *