የአለም ባንክ ለኬኒያ የ750 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ፡፡

ኬኒያ በተያዘው የፈረንጆቹ አመት ተፈጻሚ የሚሆን ብድር ከአለም ባንክ በኩል ማግኝቷን አስታውቃለች፡፡

ብድሩ ሀገሪቷ እስከ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ በአምስት ዘርፎች ላይ ለምታከናውነው ትግበራ ይውላል ተብሏል፡፡
ኬኒያ ከዚህ በፊት ያልከፈለችው ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ያለባት ቢሆንም ሀገሪቷ እያደረገች ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞ ብድሩ እንደተፈቀደላት ነው የተገለጸው፡፡

የመጨረሻ የስልጣን ዘመን እያሳለፉ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ሀገራቸው በለውጥ መንገድ እንደምትገኝ ገልጸው ባንኩ ለሀገራቸው ያጸደቀውን ብድር በተገቢው መንገድ እንጠቀመዋለን ብለዋል፡፡

ኬኒያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ አለም ባንክ እዳ ያለባት ሀገር እንደሆነች የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

ሔኖክ ወልደገብርኤል

መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *