በጎረቤት ሃገር ሱዳን በአንድ ሳምንት ዉስጥ ብቻ ከ90 በላይ ንጹሀን ዜጎች ተገደሉ፡፡

በሀገሪቷ ዛሬም በቀጠለው ግጭት ዜጎች ህይወታቸው እያለፈ ነው፡፡

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በትላንትናው እለት የ 9 ሰዎች ህይወታቸው አልፋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሁለት የጸጥታ ሀይሎች ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ጥቃት ደርሶባቸው ህይወታቸው ማለፉም ተገልጿል፡፡
ከ200 በላይ የሚሆኑ ንጹሀን ዜጎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ማስተናገዳቸውም እየተነገረ ይገኛል፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱበትን ቀን በማክበር ላይ የምትገኘው ሱዳን ዜጎቿ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡

ወታደራዊ ሀይሉ የሀገሪቷን ስልጣን ከያዘ ጀምሮ መረጋጋት የተሳናት ሱዳን በኢኮኖሚውም ክፉኛ እንደተጎዳች ነው የተባበሩት ምንግስታት ድርጅት መረጃ የሚጠቁመው፡፡

በዋና ከተማዋ ካርቱም ከትላንት ምሽት አንስቶ ለተቃውሞ የወጡ የሀገሪቱ ዜጎች ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ መግባታቸውም ተነግሯል፡፡

የጸጥታ ሀይሎችም ግጭቱን ለማርገብ አስለቃሽ ጪስ በሰልፈኞች ላይ መጠቀማቸው ነው የተነገረው፡፡

እንደ መንግስታቱ ድርጅት መረጃ እስከ ፈረንጆቹ 2022 መጨረሻ ድረስ ወደ 22 ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናዊያን ለከፋ ርሃብ ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

@ አልጀዚራ
በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *