በአዲስ አበባ የ70 አመት አዛውንት በጅብ ተበልተው ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ የ70 አመት አዛውንት ምሽት ላይ በሁለት ጅቦች መበላታቸውን የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጿል፡፡

ባለፍነው ሳምንት መጨረሻ በከተማችን አዲስ አበባ ሁለት አሳዛኝ አደጋዎች ደርሰዋል፡፡

በሁለት ጅቦች የተበሉት አዛውንት በእሳት እና የአደጋ ስጋት ሰራተኞች በተደረገላቸው እገዛ ህይወታቸውን ማትረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ የነገሩን ሲሆን አዛውንቱ በአሁኑ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል ብለውናል አቶ ንጋቱ፡፡

ከዚሁ ከድንገተኛ አደጋ ጋር በተያያዘም በመዲናዋ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሀና ጤና ጣቢያ አካባቢ በሚገኝ አንድ መኖርያ ቤት የአንድ ቀን እድሜ ያለው ህጻን ልጅ መጸዳጃ ቤት ተጥሎ ፣ ህይወቱ አልፎ መኘቱን የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ፡፡

ሚያዝያ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *