በሁሉም ዩኒየኖችና ሸማቾች በኩል ከ 30 ሺ በላይ የእርድ እንስሳት ሊቀርቡ ነው፡፡

ለመጪው የፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓላት በሸማች ሱቆችና ፤በዩኒየኖች በኩል የሚቀርቡ የእርድ እንስሳት ግዢን እየፈጸምኩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል።

ከ 500 በላይ ለቅርጫ የሚሆኑ የእርድ እንስሳትን በአሁኑ ሰዓት ግዢያቸው የተፈፀመ ሲሆን በአጠቃላይ ለመጪው የፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓላት ከ 3 ሺ በላይ የሉካንዳ ከብቶች ግዢ በአማራና በኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ የግዢው ሂደት እየተፈፀመ መሆኑን በኤጀንሲው የግብይት ዳይሬክተር ወይዘሮ ደብሪቱ ለአለም ነግረውናል፡፡
እንደ ፤ዱቄት ፤ዘይት፤በተለይ የድጎማ ዘይት፤በ148 የሸማች ህብረት ስራ ማህበራትና በሁሉም ዩኒየኖች በኩል እየገባ መሆኑን የነገሩን ወ/ሮ ደብሪቱ በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰበ ክፍሎችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማገልገል ፤መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን እያስገባን ነው ብለውናል ፡፡

እነዚህን ምርቶች የሚሰራጩት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ባዛሮችንም በማዘጋጀት፤ ለበአሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶቸን ለህረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማቅረብ እየተሰራ ይገኛል ብለውናል፡፡

ሚያዝያ 11 ቀን 2014 ዓ.ም

የውልሰው ገዝሙ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.