ወደ 2,000 የሚጠጉ የኬንያ ፖሊሶች ‘ለማገልገል አዕምሯቸው ብቁ አይደለም’ ተባለ

ወደ 2,000 የሚጠጉ የኬንያ ፖሊሶች ስራቸውን ለመስራት አእምሯቸው ብቁ አይደሉም ሲሉ የተናገሩት የሀገሪቱ የብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ሃላፊ ናቸው።

የሀገሪቱ የብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ይሄን ጉዳይ ይፋ ያደረገው በፖሊስ ሃይል ውስጥ የመንፈስ ጭንቀት እና ራስን ማጥፋት እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡

ኢንስፔክተር ጀነራል ሂላሪ ሙትያምባይ ዛሬ ኤጲስ ቆጶሳት እና ከፍተኛ ቀሳውስት በተገኙበት መድረክ እንደተናገሩት ሁሉንም የፖሊስ መኮንኖች በህክምና ከመረመሩ በኋላ “አስደንጋጭ” የውስጥ ችግሮች ፖሊሶቹ ላይ እንዳገኙባቸው ተናግረዋል ።
ኬንያ በብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት ስር የሚሰሩ 100,000 የሚያህሉ የፖሊስ መኮንኖች አሏት።

ሚስተር ሙትያምባይ አንዳንድ የተጎዱ የፖሊስ መኮንኖችን ከስራ የማስወጣት ሂደቱን መጀመራቸውን ገልፀው የአእምሮ ጤንነት ያላቸው ፖሊሶች መኖራቸው አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

“የእኛ የስራ መሳሪያ ሽጉጥ ነው፣ እና አንድ ጥይት ሲተኮስ፣አንድምታው ከባድ ነው” ብለዋል.
ይሁንና ፖሊሶቹን ከሥራ ማባረር ቀላል እንዳልሆነ የገለጹ ሲሆን በሂደት ላይ ያሉ በርካታ ሥራዎችም አሉ ብለዋል፡፡።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፖሊስ መኮንኖች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ስጋቶች እየጨመሩ መጥተዋል እናም መንግስት ጉዳዩን ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉም ተናግረዋል

ፖሊስ አሁን የአእምሮ ጤና አገልግሎት ለመስጠት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድጋፍ አማካሪዎችን እና የስነ-አእምሮ ባለሙያዎችን ያካተተ የባለሙያ የጤና ቦርድ ስራ እንዲጀምር አድርጓል ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሔኖክ አስራት

ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.