የሶማሊያ ፓርላማ ሼክ አዳን ሞሃመድ ኑርን አዲሱ አፈ-ጉባኤ አድርጎ መረጠ፡፡

የሶማሊያ ህግ አዉጭዎች ለቦታዉ ትክክለኛዉ ሰዉ የትኛዉ ነዉ በሚለዉ ሃሳብ ላይ ባለመግባባት ብዙ ቢቆዩም፣ በመጨረሻም ሼክ አዳን ሞሃመድ ኑርን አፈ-ጉባኤ አድርገዉ መርጠዋል፡፡

ይህ የፓርላማ እና ሴኔት የአፈ-ጉባኤ ምርጫ ሶማሊያ እየመሰረተች ላለችዉ አዲስ መንግስት ቁልፍ መንገድ ነዉ ያለዉ የዓለም የገንዘብ ፈንድ /IMF/፣ ሶማሊያ በጀት እንዲለቀቅላት የምትፈልግ ከሆነ በተባለዉ ጊዜ ማለትም የፊታችን ግንቦት 17 የመንግስት ምስረታዉን ማድረግ አለባት ብሏል፡፡

በአክራሪዎች ጥቃት እና የፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፎርማጆ እና የጠቅላይ ሚኒስቴር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ የስልጣን ሽኩቻ፣ የሶማሊያ ምርጫ እንዲራዘም ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሁለቱም መሪዎች በትዊተር ገጻቸዉ ለአዲሱ አፈ-ጉባኤ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሞሀመድ ሮብሌ፣ ፖሊስን እና የደህንነት ሃላፊዎችን በተራዘመዉ ምርጫ ጉዳይ እጃቸዉን እንዳያስገቡ ይልቁንም የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ለህግ አዉጭዎቹ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸዉ የአፍሪካ ህብረትን ጠይቀዋል፡፡

ባለፈዉ ዓመት የነበረዉ የፖለቲካ ሽኩቻ ወታደሩ በሶማሊያ ሞቃዲሹ ያሉ ወሳኝ ቦታዎችን እንዲቆጣጠር አድርጎት ነበር፡፡

ከዓመት በፊት የተራዘመዉ የሶማሊያ ምርጫ ፓርላማዉን ባስቆጣ የፕሬዝዳንት ሞሃመድ ፎርማጆ የአራት ዓመት የስልጣን ቆይታን በተጨማሪ የሁለት ዓመት ግዜ ለማራዘም በተደረገ ጥረት መዘግየቱም ይታወቃል፡፡

ማክሰኞ ዕለትም የረጅም ግዜ ሴናተር እና የፕሬዝዳንቱ ቀንደኛ ነቃፊ የሆኑት አብዲ ሃሺ በድጋሚ ለታችኛዉ ምክርቤት አፈጉባኤ ሆነዉ ተመርጠዋል፡፡

@ሮይተርስ

በእስከዳር ግርማ

ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *