‹‹በአሁኑ ሰዓት ያለው የደም ክምችት ከአምስት ቀናት በታች የሚያገለግል ነው››… ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት፡፡

በአሁኑ ሰዓት ያለው የደም ክምችት ከአምስ ቀን በታች ብቻ የሚያገለግል ነው ሲል የብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
በቀይ መስቀል ከፍተኛ የደም እረት መከሰቱንም በብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የኮሚውኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

እጥረቱ ለመከሰቱ አንዱ ምክንያት ወቅቱ የበዓል እና የፆም ወቅት በመሆኑ እንደሆነ ዶ/ር ተመስገን አንስተዋል፡፡

የተከሰተዉ እጥረት እንደየ የደም አይነቱ የሚለያይ ቢሆንመን ፕላትሌት የተሰኘው የደም አይነት ለአንድ ቀን ብቻ የሚያገለግል ክምችት ነው ያለው ፤ የደም አይነት “O” ደግሞ ክምችቱ ለሁለት ቀናት የሚሆን ብቻ ነው ያለው ብለውናል።

በደም ባንክ የደም እጥረት ሲያጋጥም በየ ሆስፒታሎች ደግሞ የደም ፍላጎት መጨመር እንደሚኖር የገለፁት ዶ/ር ተመስገን፣ በዚህም በፍጥነት አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው ታካሚዋች መደራረብን ያመጣል ብለዋል።
ለዚህም ሲባል ተቋሙ በቀጣይ ቀናት በዘመቻ መልክ የደም ማሰባሰብ ለማድረግ ማቀዱን አንስተዋል።

በተለይም በክልሎች ያለው የደም ልገሳ ልምድ ዝቅተኛ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ተመስገን ያለዉን ክምችት ከፍ ለማድረግ ደም መስጠት የሚችል የትኛዉም ሰዉ የደም ልገሳዉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 01 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *